Mereb.shop Home Page
 
 
Hello. Sign in. New customer? Start here.
Gift Central | Gift Card | Your Account
 
Search 
Books Eth. Orthodox Tewahedo Church Fiction & Fantasy Children's Books History Biographies and Memoirs
         
Kegn Geta Yoftahe Niguse (Achir  YeHywetuna YeTsuhufu Tarik)
See larger image views

Kegn Geta Yoftahe Niguse (Achir YeHywetuna YeTsuhufu Tarik) (Paper Cover)
ቅኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ)

~ Yohannes Admasu (Author)
More about this product
Share on FacebookShare with your friends on Facebook
 
Price: $14.65
 
Usually ships in 1-2 days
Ships from and sold by Mereb.shop.
 
Sign in for Express Checkout to speed up your ordering and to view shipping & handling price here before checkout.
 
Ready to buy?
Price: $14.65
 
Quantity:

 
Share with friends
  E-mail Facebook Twitter  
 
Product Description

ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ

ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም።

የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል፡፡ ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል።

የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ የድርሰት ሥራዎች 

ተአምራዊው ዋሽንት (፲፱፻፳፫ ዓ/ም)
ጎበዝ አየን (፲፱፻፳፰ ዓ.ም.) * ምስክር (፲፱፻፴ ዓ/ም)
ጥቅም ያለበት ጨዋታ (፲፱፻፴፩ ዓ/ም)
ሙሽሪት ሙሽራ
ያማረ ምላሽ
የሆድ አምላኩ ቅጣት (፲፱፻፴፪ ዓ/ም)
ዳዲ ቱራ (፲፱፻፴፫ ዓ/ም)
የህዝብ ጸጸት (፲፱፻፴፬ ዓ/ም)
ሙሾ በከንቱ (፲፱፻፴፭ ዓ/ም)
አባት ንጉሳችን ጠረፍ ይጠብቅ (፲፱፻፴፭ ዓ/ም)
የደንቆሮዎች ቲያትር (፲፱፻፴፮ ዓ/ም)
አፋጀሽኝ (፲፱፻፴፮ ዓ/ም)
ዓለም አታላይ (፲፱፻፵፩ ዓ/ም)
እያዩ ማዘን (፲፱፻፵፪ ዓ/ም)
ንጉሡ እና ዘውዱ (፲፱፻፵፮ ዓ/ም)

ምንጭ የጽሀፊ ትዕዛዝ አክሊሉ የፌስ ቡክ ገጽ

Sample Pages
Browse Sample Pages:
Click on the following links to get detail view.
Table Of Content
Introduction
Preface
About the Book
About the Author
Back Cover (Sample from the Book)

Are you copyright owner of this book? You can improve this page by providing sample content for customers to have more idea on your book. Please contact us for more detail on how to work out on this.

Table Of Content
 

Copyright Complaints
Mereb respects the intellectual property of others. If you believe that your work has been copied in a way that constitutes copyright infringement, please follow our Notice and Procedure for Making Claims of Copyright Infringement.

Product Details
  Author: Yohannes Admasu
  Paper Cover: 321 pages
  Publisher: Addis Ababa University Press (2012)
  Language: Amahric
  ISBN-13: 978-99944-52-49-1
  Product Dimension: 6.12 x 9.12 x 0.9 Inches
  Shipping Weight: 744 Grams (View shipping rates and policies)
  Note: Gift-wrapping is not available for this item.
  MPID: 5920655294
  Availability: Usually ships in 1-2 days
 
 
 
 
Mereb.shop Home   |   Directory of All Stores
Business Programs: Sell on Mereb   |   Join Affilates   |   Advertise With Us
View Cart   |   Your Account   |   Contact Mereb   |   Conditions of Use   |   Returns Policy   |   Privacy Policy
Copyright © 2024 Mereb Inc. All Rights Reserved.
Designated trademarks and brands are the property of their respective owners.